ዋሺንግተን ዲሲ —
የትግራይ ኃይሎች ላሊበላ ከተማን መቆጣጠራቸውን ሁለት የዐይን ምስክሮቹን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገበ።
ሮይተርስ የዐይን ምስክሮቹ የገለጹለትን በነጻ ምንጭ በኩል ለማረጋገጥ እንዳልቻለ አመልክቷል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከኢትዮጵያ የጦር ኃይል እና የትግራይ ክልልን ጉዳይ ከሚመለከተው የመንግሥት ግብረ ኃይል ለዚህ ዘገባ ምላሽ እንዳላገኘም አስታውቁዋል።
ከደቂቃዎች በፊት የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ማንደፍሮ ታደሰ ያሉበት ቦታ ለደህንነታቸው አስጊ መሆኑን ገልጸው ነገር ግን የህወሓት ታጣቂዎች ገነተ ማሪያም ተብሎ በሚጠራው መግቢያ በኩል ላሊበላ መግባታቸውን አረጋግጠዋል።
ታጣቂዎቹ ከተማዋን ሲቆጣጠሩ ምንም አይነት ውጊያም ሆነ ተኩስ እንዳልነበረ ለቢቢሲ የተናገሩት ትክክለኛ የእርሳቸው ቃል መሆኑንም አረጋግጠውልናል።
በነገ ምሽት ዝግጅታችን ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን።