በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፣ በትግራይ ክልል የሶስት ቀናት ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ትላንት ሰኞ አመሻሹ ላይ መቀሌ የገቡት የአምሳደር ማሲንጋ ጉብኝት፣የፕሪቶሪያውን ስምምነት ውጤታማ አተገባበር በማረጋገጥ እና ፖለቲካዊ አለመግባባቶችን በውይይት የመፍታትን አስፈላጊነት በማጉላት ላይ ያተኮረ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።
አምባሳደሩ በዛሬው ውሏቸው፣ በኤምባሲው ድጋፍ ጥገና የተደረገለትንና በክልሉ ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ የሚገኘውን የአቡነ አብርሃም ገዳም ጎብኝተዋል።
መድረክ / ፎረም