ትግራይ ክልል ውስጥ ዐድዋ ከተማ፣ አንዲት አዳጊን አግተው በመውሰድ መግደላቸው በፍርድ ቤት ተረጋግጦ “ጥፋተኛ” የተባሉ ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው በሞት አንደኛው ደግሞ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ፣ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዋለው ችሎት ፈረደ።
Embed
share
The code has been copied to your clipboard.
The URL has been copied to your clipboard
No media source currently available
ቀጥተኛ መገናኛ
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ዐድዋ ከተማ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከቤት ወጥታ የቋንቋ ትምሕርት ወደ ምትከታተልበት ትምሕርት ቤት በማምራት ላይ የነበረችን አንዲት አዳጊ፣ በተለምዶ ባጃጅ ተብሎ በሚጠራ ባለ ሦስት እግር ተሽከካሪ በመጠቀም አግተው ወስደዋታል፣ በኋላም ገድለዋታል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ተከሳሾች ዛሬ ተፈርዶቻቸዋል።
የመቐለ ዞን ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኞ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ የ16 ዓመት አዳጊ ማኅሌት ተኽላይን በመግደል ተከሰውና ጥፋተኛ ተብለው የፍርድ ውሳኔያቸውን ለመጠባበቅ ለዛሬ ተቀጥረው ከነበሩት ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው የ24 ዓመት ዓወት ነጋሲ ሓጎስ ሞት ሲፈረድበት፣ ሁለተኛው የ20 ዓመቱ ናሆም ፍፁም ኃይሉ ደግሞ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም