በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ጦርነት ያስተጓጎለውን ትምህርት ለማስጀመር እንደሚሠራ ሚኒስቴሩ ገለጸ


በትግራይ ጦርነት ያስተጓጎለውን ትምህርት ለማስጀመር እንደሚሠራ ሚኒስቴሩ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:31 0:00

በትግራይ ክልል ትምህርት በአፋጣኝ ለመጀመር እንዲቻል እየሠራ መኾኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶር. ሳሙኤል ክፍሌ የመሩት የፌዴራል መንግሥት ልኡክ፣ በትግራይ፣ ትምህርት በአፋጣኝ ስለሚጀመርበት ጉዳይ፣ ከክልሉ አመራሮች ጋራ በመቐለ ከተማ ውይይት አካሒዷል።

ሚኒስትር ዲኤታው፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራርያ፣ በትግራይ ክልል፣ በአፋጣኝ ትምህርት ለመጀመር በሚቻልባቸው ተቋማት ትምህርት እንዲጀመር ጥናት በመካሔድ ላይ እንዳለ ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሓላፊ፣ ዶር. ኪሮስ ጉዕሽ በበኩላቸው፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሠራቸው ጉዳዮች አንዱ፣ የመማር ማስተማሩን ማስጀመር ነው፤ ብለዋል።ይኹንና ኹለቱም አመራሮች፣ በትግራይ፣ ትምህርት የሚጀመርበትን ቁርጥ ያለ ቀን አልገለጹም።

በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG