No media source currently available
የትግራይ ክልል ከሌላው ኢትዮጵያ ተለይቶ ያካሄደውን ምርጫ ያሸነፈው ህወሓት በዛሬው ዕለት በክልሉ አዲስ መንግሥት መስርቷል። በዚህ ምስረታ የክልሉ አዲስ ምክርቤት ሥራ የጀመረ ሲሆን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙትዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤልም ቃለ መሓላ ፈፅመዋል። የኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት እንደ አዲስ የሚስተካልበት ግዜ ደርሷል ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።