No media source currently available
ህወሓት በአሁኑ ወቅት ህዝብን ከህዝብ ላማጋጨትና ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው ሲሉ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ሊቀመንበር ተናገሩ፡፡ “ተከበሃል” በሚል ቅስቀሳም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊት እየመለመለና ተጨማሪ የጦር ሰፈሮች እየከፈተ ነው ሲሉም ከሰዋል፡፡ ከህወሃት ወገን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡