በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ሥራ አስጀመረ


ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ሥራ አስጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:27 0:00

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከሦስት ዓመታት መስተጓጎል በኋላ፣ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኘውን ቢሮውን፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሳቢያ ከተዘጋ ከሦስት ዓመታት በኋላ በዛሬው ዕለት ከፍቶ ሥራ ሲያስጀምር፣ ወደ ክልሉ የላካቸው ባለሞያዎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋራ ተነጋግረዋል። የቦርዱ ባለሞያዎች ቡድን፣ ከብዙኃን መገናኛ እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራም ተወያይተዋል::

ከውይይቱ ተሳታፊዎች አንዱ፣ የትግራይ ክልል የሲቪል ማኅበረሰብ ኅብረት ሥራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ በርኸ፣ ጅማሬውን አድንቀዋል። ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በኋላ፣ አገራዊ ተቋማት፣ በትግራይ ክልል ሥራ እየጀመሩ መኾናቸውን ሥራ አስኪያጁ ጠቅሰው፣ ይህም ሰላሙ ዘላቂ እንዲኾን የሚያግዝ ነው፤ ብለዋል::

በትግራይ ክልል፣ ምርጫ ለማካሔድ የሚቻልበትን ኹኔታ አስመልክቶ፣ ዳሰሳዊ ውይይት በተካሔደበት ጊዜ፣ ሕዝቡ በመረጠው መንግሥት መተዳደር እንደሚፈልግ መነሣቱን የተናገሩት አቶ ያሬድ፣ በአፋጣኝ መፈታት የሚኖርባቸውም ጉዳዮች ተለይተው መታየታቸውን ገልጸዋል::

በሌላ በኩል፣ ትላንት ግንቦት 2 ቀን፣ የ2015 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የአፈጻጸም ሪፖርቱን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ፣ በትግራይ ክልል እና በጸጥታ ምክንያት ስድስተኛው ዙር አገራዊ ምርጫ ባልተካሔደባቸው ሌሎችም አካባቢዎች፣ በሚቀጥለው 2016 ዓ.ም. ምርጫ ለማካሔድ መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡

በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ፣ የትግራይ ክልልን ጨምሮ ምርጫ ያልተካሔደባቸው፣ 96 የምርጫ ክልሎች እንዳሉ ቦርዱ ገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG