የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዓለም ይሕደጎ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ የማዋሐድ እና የማቋቋም ሒደትን ለማስጀመሪያ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፣ በመጪዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ፣ በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀብት ማሰባሰብ ሥራ ይፈጸማል፤ ብለዋል።
በሌላ ዜና፣ በብልጽግና ፓርቲ እና በህወሓት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በመቐለ ከተማ ለሦስተኛ ጊዜ ትላንት ረቡዕ ተካሒዷል።