በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

75ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን በማሰናበት ሥራ እንደሚጀመር የተሐድሶ ኮሚሽኑ ገለጸ


75ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን በማሰናበት ሥራ እንደሚጀመር የተሐድሶ ኮሚሽኑ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን አደረጃጀት በማፍረስ ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው የመመለስ ሥራ፣ ከሁለት ወራት በኋላ እንደሚጀምር ያስታወቀው የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን፣ በመጀመሪያው ዙር 75ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን እንደሚያሰናብት ገልጿል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዓለም ይሕደጎ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ የማዋሐድ እና የማቋቋም ሒደትን ለማስጀመሪያ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፣ በመጪዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ፣ በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀብት ማሰባሰብ ሥራ ይፈጸማል፤ ብለዋል።

በሌላ ዜና፣ በብልጽግና ፓርቲ እና በህወሓት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በመቐለ ከተማ ለሦስተኛ ጊዜ ትላንት ረቡዕ ተካሒዷል።

XS
SM
MD
LG