በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር፣ የክልሉ ማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን መዓሾ እሁድ ኅዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ከአክሱም ወደ መቐለ እየተጓዙ በነበሩበት ወቅት፣ ማይቅነጣል በተባለ አከባቢ በተከፈተባቸው ተኩስ ተሽከርካሪያቸው ላይ ጉዳት መድረሱን ተናገሩ።
አቶ ሰሎሞን ጥቃቱ በመኪናቸው ላይ መድረሱና፣ ጉዳቱንም በፎቶ ማስረጃ አስደግፈው እንደያዙት ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸው ለተጨማሪ ጥያቄዎቻችን መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የማይቅነጣል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ “መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም” ብለዋል።
ከክልሉ ጸጥታ እና ሰላም ቢሮ እንዲሁም የኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኝት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
መድረክ / ፎረም