በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቲቦር ናጂ ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ኬንያንና ጀርመንን ይጎበኛሉ

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጂ
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጂ

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጂ ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ እአአ እስከ ታህሳስ 8 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ኬንያንና ጀርመንን እንደሚጎበኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ገልጿል።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጂ ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ እአአ እስከ ታህሳስ 8 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ኬንያንና ጀርመንን እንደሚጎበኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ገልጿል።

በጉብኝታቸው ወቅት የሚያተኩሩት በዩናይትድ ስቴትስና በአፍሪካ መካከል የንግድ ግንኙነት እንዲጠነክር፣ የአፍሪካ ወጣቶች መሰረትን መገንዘብ፣ በአጋርነት በኩል ሰላምና ፀጥታ እንዲዳብር እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ህዝብና ሃገሮች ባላት ቁርጠኝነት በማስመር ላይ መሆኑ ናጂ አስረድተዋል።

በአፍሪካው ጉብኝታቸው ወቅት ከመንግሥት ባለሥልጣኖች፣ ከንግድ መሪዎችና ከወጣት አፍሪካውያን መሪዎች መርኃ ግብር ተሳታፊዎች ጋር እንደሚነጋገሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ ገፅ ላይ የወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG