በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት ከሦስት ኢዮጵያውያን ምሑራን ጋር (ክፍል አንድ)


አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣ ዶ/ር ደረሰ ጌታቸውና ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ
አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣ ዶ/ር ደረሰ ጌታቸውና ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ

የሕግ ባለሞያው አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣ የኒዩርክ አዮና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ደረሰ ጌታቸውና ከሜልበርን ዩኒቨርሲቲ ሕግ ፋካልቲ ሪሰርቸር ረዳት መምህር ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ናቸው ተወያዮቹ ። ያወያየቻቸው ደግሞ ጽዮን ግርማ ናት።

በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አንድ ዓመት ሊያስቆጥር ጥቂት ቀናት ይቀሩታል። እንዲሁም በአማራ፣ በኮንሶ እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እና ተቃውሞውን ለመበተን የሚወሰደው እርምጃ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።

ይህንን ጉዳይም ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛን ጨምሮ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተሉ ሁሉ እየዘገቡት ይገኛሉ። እሁድ ዕለት በቢሾፍቱ ሆራ ሃይቅ ኢሬቻ በዓል ላይ በተከሰተው አደጋ ደግሞ የበርካቶች ሕይወት ጠፍቷል። ይህንንና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሕግ ባለሞያው አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣ የኒዩርክ አዮና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ደረሰ ጌታቸውና ከሜልበርን ዩኒቨርሲቲ ሕግ ፋካልቲ ሪሰርቸር ረዳት መምህር ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ናቸው ተወያዮቹ ። ያወያየቻቸው ደግሞ ጽዮን ግርማ ናት።

የመጀመሪያው ክፍል ዛሬ ይቀርባል። ውይይቱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ውይይት ከሦስት ኢዮጵያውያን ምሑራን ጋር(ክፍል አንድ)
please wait

No media source currently available

0:00 0:32:37 0:00

ውይይቱ ተጀመረ እንጂ አላበቃም። የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ምን ይመስላል? ካሁን በኋላ ምን ይጠበቃል?ምን ዓይነት ስጋት አለ? ችግሮችን ለመፍታት ምን መደረግ አለበት? ለተወያዮቹ የተነሱ ጥያቄዎችና የተወያዩበት ጉዳዮች ናቸው። ሁለተኛውና የመጨረሻው ክፍል ቅዳሜ ምሽት ይቀርባል።

በተጨማሪም ለሚነሱት ጥያቄዎች የኢትዮጵያ መንግሥትን ምላሽ ለማካተት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተወያይ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ መሐምድ ሰኢድ ስብሰባ ላይ መሆናቸውን በመግለፃቸው ማካተት አልቻልንም። ነገር ግን ውይይቱ እንደተጠናቀቀ የኢትዮጵያን መንግስት ምላሽ አካተን እንዲሁም እናንተም አድማጮች ውይይቱን ተከታተላችሁ የምትሰጡትን አስተያየት ጨምረን ውይይቱን እንቀጥላለን።

በውይይቱ ላይ ያላችሁን ጥያቄዎች እንዲሁም በቀጣይ ከዚህ ጉዳይ ጋር መነሳት አለበት የምትሉትን ሁሉ ፃፉልን። በቀጣይ በምናደርገው ውይይት ሐሳባችሁን ለማካተት ጥረት እናደርጋለን።

XS
SM
MD
LG