አዲስ አበባ —
ሰሞኑን በጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ሰብሳቢነት የተካሄደው የፓርቲዎች ውይይት በምርጫ ቦርድ መሪነት እንደሚቀጥል የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የጠሚኒስትሩ ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ዛሬ ለጋዜጠኞች እንዳሉት ውይይቱ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው፡፡
የሕግ የበላይነትን ማስከበር መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ የማሻሻያ እርምጃዎች ወሳኝ አካል መሆኑን የገለፁት የፕሬስ ኃላፊዋ ከዚህ ውጭ የሚንቀሳቀሱትን እንደማይታገስም ተናግረዋል፡፡
የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ዛሬ የሰጡትን መግለጫ የተከታተለው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ዘገባ ልኳል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ