No media source currently available
ኢትዮጵያን ዘመናዊ ዴሞክራሲያዊ ሀገር አርጎ ለማቆም ሲካሄድ በኖረው ትግል ቀጣዩ ምርጫ ትክክለኛ የፖለቲካ አቅጣጫ ሊያስገኝ እንደሚችል ተጠቆመ። ይህንን ውጤት ዕውን ለማድረግ ግን ህዝቡና የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ብርቱ ሥራ በጥንቃቄ መሥራት በእጅጉ አስፈላጊ ነው ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አስገነዘቡ፡፡