ለንደን —
ሚስ ማርጋሬት ታቸር በግርማዊት ንግሥት ኤልሣቤጥ “እመቤት ሆይ” – “ባሮነስ” የሚል በእንግሊዝ ዘውዳዊ ሥርዓት የክብር ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡
እመቤት ሆይ ማርጋሬት ታቸር በፖለቲካ ሕይወታቸው ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ሆነው ነው ያለፉት፡፡
እአአ ከ1979 እስከ 1990 ዓ.ም በዘለቀው የመራኂ-መንግሥትነት ዘመናቸው በወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው “ፀረ-ማኅበራት፣ መንግሥታዊ ቁጥጥር ጠል አመራር የእንግሊዝን ምጣኔ ኃብትና ኅብረተሰብ አቅጣጫና ሕይወት ለውጠዋል” እየተባለ ይወራላቸዋል፡፡
ባሮነስ ማርጋሬት ታቸር፤ የአንድ ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ባለቤት ልጅ ማርጋሬት ሮበርትስ - እነሆ የእንግሊዝ የመጀመሪያዋ፣ እስከዛሬም ብቸኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ትሆን ዘንድ አደገች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸር መንግሥታቸውን እርሣቸው በሥልጣን ላይ ለቆዩባቸው ዓመታት ያህል ለረዘመ ጊዜ የተጓዙ በሃያኛው መቶ ክፍለዘመን ለእንግሊዝ ብቸኛዋ ናቸው፡፡
ወደጠቅላይ ሚኒስትርነቱ በዘለቁ ጊዜም ተስፋቸውን ሲናገሩ፡- “ምሥቅልቅል ባለበት የሠመረ መጣጣምን እናምጣ፣ ስህተት ባለበት ዕውነትን እናምጣ፣ መጠራጠር ባለበት ዕምነትን እናምጣ፣ ተስፋ መቁረጥ በነገሠበት፣ ተስፋን እንፈንጥቅ” ብለው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ማርጋሬት ታቸር በሦስት ተከታታይ የምርጫ ዘመናት አሸንፈው እንግሊዝን ሲያስተዳድሩ “ሠራተኞችን አግልለው፣ የጤናውን አገልግሎትና ጉዳት አምጭ አቅርቦቶችን ቁጥጥር አጥፍተው፣ የራሣቸውን ካቢኔም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከፋፍለው ጉልህ የሆነ ምሥቅልቅል ፈጥረዋል” እያሉ የሚተቹ የፖለቲካ አቃቂረኞች አሉ፡፡
የሰሜን አየርላንድን ታጣቂዎች “ሰጥ አድርገው ይዘዋል” የተባሉ፤ በፎክላንድ ደሴቶች ጉዳይ ውቅያኖስና ባሕሮች አቋርጠው ከአርጀንቲና ጋር ጦር የገጠሙ፣ እንግሊዝን የአውሮፓ ኅብረት አባል ያደረጉ፣ ዩሮንና ክፍት ድንበርን ግን የተቃወሙ ብዙ ሌሎችም ተግባራት --- ለጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸር በታሪክ ተፅፈው ይገኛሉ፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
*** በነገራችን ላይ ዛሬ የዓለም መዝናኛ የሆነውን አይስ ክሪም እንዲህ ዛሬ እንደምንጠቀምበት እድርጋ የፈጠረችው አንዲት ማርጋሬት ሮበርትስ የምትባል ወጣት ኬሚስት እንደነበረች ያውቁ ኖሯል? ይህቺ “አይስክሪም ገርል” ነች በጊዜ ጉዞ ውስጥ ወደ “አይረን ሌዲ”ነት የተለወጠችው፡፡ ኬሚስት ሮበርትስ ዲሴምበር 13/1951 ዓ.ም ዴኒስ ታቸርን አገባችና ማርጋሬት ታቸር ሆነች፡፡ የመንትያ ወንድ ልጆች እናት፣ ሙዚቃ አፍቃሪና ፒያኖ ተጫዋች፣ የሕግ ባለሙያ፣ ፖለቲከኛ፣ የቤት እመቤትና ጠቅላይ ሚኒስትር፡፡ ***