በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የህሙማን እና የአዛውንቶች ማዕከል የከፈቱት ወጣቶች አገልግሎታቸው


Grace Nursing home
Grace Nursing home

ሕክምና አጥንቶ ስራ አጥ መሆን ከባድ ነው የምትለው ዶ/ር ጽዮን ሰለሞን ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊት የቤት ለቤት የሕክምና አገልግሎት ትሰጥ ነበር፡፡ ወረርሽኙ፣ በቤት ለቤት አገልግሎት ወቅት የታዘበቻቸው የአስታማሚዎች ችግር የህሙማን በቂ የሆነ ድጋፍ አለማግኘት ከአጋሯ ዶ/ር ናትናኤል ሃይሉ ጋር ግሬስ የሕሙማን እና የአረጋዊያን እንክብካቤ ማዕከልን እንዲመሰርቱ ገፋፋቸው፡፡

ይሄ በአይነቱ የመጀምሪያው የሆነው ማዕከል ከሆስፒታል ውጭ ሆነው ነገር ግን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እንዲሁም ለአረጋዊያን በነርሶች የተደገፈ እርዳታን ይሰጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዘመናዊ ሕይወት ምክንያት ያጡትን ጉርብትና እና መቀራረብ እንደፈጠረ ዶ/ር ጽዮን ትናገራለች፡፡

በዚህ ማዕከል ውስጥ የቤተሰብ አባላቸውን ለማስታመም ያስገቡት ዶ/ር አታክልቲ በራኪ "ከሁሉ ያስደሰተኝ ማዕከሉ በባለሞያዎች መመራቱ እና ከባድ ነገር ቢመጣም ከከፍተኛ የህክምና ማዕከላት ጋር ትስስር ስላለው ነው" ይላሉ፡፡ ዶ/ር አታክልቲ ይህን መሰል ነገር በውጪ ሃገር በነበሩበት ሰዓት ማየታቸውን በመግለጽ ይሄ አገልግሎት በኢትዮጵያም መጀምሩ ይበል የሚያስብል ነው ይላሉ፡፡

ልክ እንደሳቸው ሁሉ እናታቸውን በማዕከሉ ያስገቡት ወ/ሮ ሃና ተስፋሚካኤል በትምህርት እና በስራ ከተጨናነቀው ጊዜያቸው ቀንሰው እናታቸውን ቢንከባከቡም እናታቸው ግን ብቻቸውን እቤት መዋላቸው የብቸኝነት ስሜት በማሳደር ትልቅ ተጽእኖ አሳድሮባቸው እንደነበረና አሁን ላይ ግን ይሄ መቀረፉን ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የህሙማን እና የአዛውንቶች ማዕከል የከፈቱት ወጣቶች አገልግሎታቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:27 0:00


XS
SM
MD
LG