No media source currently available
ግሬስ የህሙማን እና የአዛውንቶች እንክብካቤ ማዕከልን እንድንከፍት ያደረገን ኮቪድ 19 ነው የምትለው ከመስራቾቹ መሃከል አንዷ ዶ/ር ጽዮን ሰለሞን ናት፡፡ ማዕከሉ አዛውንቶች እና ከሆስፒታል ውጭ እንክብካቤ የሚያሻቸው ታማሚዎች በነርሶች እየታገዙ እንዲታከሙ እንዲሁም ማህበራዊ ህይወታቸውን እንዲገፉ ያግዛል፡፡ በተለይም ስራ እና ትምህርት ኖሯቸው የሚወዷቸውን ማስታመም ያልቻሉ ሰዎች በማዕከሉ ስላገኙት ጥቅም አነጋግረናቸዋል፡፡