ዋሽንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጠሩትና ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ሐሙስ፤ ኅዳር 30 እና ዓርብ፤ ታኅሳስ 1/2014 ዓ.ም. እየተካሄደ ያለው ዓለምአቀፍ የዴሞክራሲ ጉባዔ መሠረታዊ ዋልታዎች ዴሞክራሲን ማጠናከርና አምባገነናዊነት እንዳያጠላበት መጠበቅ፣ ሙስናን መዋጋት፣ የሰብዓዊ መብቶች መከበርን ማበረታታት እንደሆኑ ተገልጿል።
በጉባዔው ላይ እንዲሳተፉ ከመቶ በላይ ሃገሮች ተጋብዘዋል። 17ቱ የአፍሪካ ሃገሮች ናቸው። ኢትዮጵያ አልተጋበዘችም። አትሳተፍምም። ለመሆኑ ለአሜሪካም ይሁን ለሌሎች ሃገሮች መድረኩ ምን ትርጉም አለው? የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና የፖለቲካ ሣይንስ አዋቆች የሚያስቡትን ለአሜሪካ ድምፅ ታዳሚ ያጋራሉ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።