ለንደን —
በ87 ዓመት ዕድሜአቸው ባለፈው ሣምንት ያረፉትን የቀድሞዋን የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸርን የአደባባይ የክብር አሸኛኘት ለመከታተል በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ዛሬ በለንደን አደባባዮች ላይ ተኮልኩለው ውለዋል፡፡
የሚስ ታቸር አስከሬን ያረፈበትን ሣጥን የተሸከመው የፈረስ ሠረገላ በለንደን ጎዳና ሲያልፍ የመጨረሻውን ክብር ሊገልጥ ግራና ቀኙን የቆመው ሰው ብዙ ነበር፡፡
የማርጋሬት ታቸር አስከሬን ከፀጥታ ጥበቃው ሌላ በክብር ዘብ አባላትና በወታደራዊ ክፍሎችም የታጀበ ነበር፡፡
በለንደን አደባባዮች ዛሬ የወጣው ሰው ክብርና ፍቅሩን የሚገልጥ ብቻም አልነበረም፡፡
ተቃውሞና ቁጣም የነበረባቸው አብረው ሰልፉ ላይ ውለዋል፡፡
ሣጥናቸው ባረፈበት ቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል ውስጥ ሁለት ሺህ ኀዘንተኞችና የታቸር አፍቃሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የአሁኑ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምረን፣ ከዓለም ዙሪያም ለንደን የገቡ የዛሬና የቀደሙ መሪዎችም በሥፍራው ነበሩ፡፡ በፎክላንድ ደሴቶች ምክንያት እአአ በ1982 ዓ.ም ጦር ከገጠሟት አርጀንቲና ግን አንድም ባለሥልጣን አልተገኘም፡፡
በፀሎቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተናገሩት የለንደን ጳጳስ ሪቻርድ ቻርትረስ ባሰሙት ቃል እንዲህ አሉ፤ “በጋለ የፖለቲካ እንካሰላንቲያ ውስጥ ከዘለቀ የሕይወት ማዕበል ባሻገር፣ እነሆ ታላቁ ፀጥታ ሠፍኗል፡፡ ….”
ለተጨማሪና ለዝርዝር የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ