በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቴክሳስ ከት/ቤቱ የጅምላ ጥቃት በኋላ ብሄራዊ የመሳሪያ ማኅበሩ ጉባኤውን ከፍቷል


ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ በሚገኝ አንድ ትምርህ ቤት ውስጥ 19 ህጻናትና 2 መምህራንን ጨምሮ 21 ሰዎች ከተገደሉበት ጥቂት ቀናት በኋላ ዛሬ ዓርብ እዚያው ቴክሳስ ሂውስተን ውስጥ ብሄራው የመሳሪያ ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤውን እያካሄደ መሆኑን ተገለጸ፡፡

የቴክሳስ አገረ ገዥ ግሬግ አቦት በጉባኤው ላይ ንግግር ያሰማሉ ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ወደዚያ ከማምራት ይልቅ ወደ ግድያው ወደ ተፈጸመባት ዩቫልዲ እንደሚያቀኑ ተገልጿል፡፡ አገረ ገዥው በማህበሩ ስብሰባ ላይ በቪዲዮ የተቀረጸ መልዕክታቸውን እንደሚያሰላለፉ ዳላስ ሞርኒንግ ኒውስ ዘግቧል፡፡

የቀድሞ የዩናይትድ ሰቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር እንደሚያሰሙ በመርሃ ግብሩ ላይ አሁን ድረስ የተካተተ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ የቴክሳስ ህግ አስከባሪዎች ባላፈው ማክሰኞ በ18 ዓመቱ ወጣት የጅምላ ግድያው በተፈጸመበት ወቅት፣ በሥፍራው ተገኝተው ስለጡት ምላሽና በቦታው ለመድረስ ስለ ወሰደባቸው ጊዜ ጠንካራ ጥያቄዎች እየገጠማቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባለሥልጣናት እንደተናገሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያቋረጠው አጥቂው ራሞስ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ሆኖ 21 ሰዎችን ለመግደል፣ ከ40 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ያህል ጊዜ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG