አዲስ አበባ —
በሳክስፎኒስትና በፒያኒስትነት የሚታወቀው ተፈራ አቡነወልድ በ1939 ዓ.ም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትን ከተቀላቀለ ጀምሮ ከሰድሣ ዓመታት ላላነሰ ጊዜ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ የተካፈለና ተፅዕኖም ያሣደረ ሙዚቀኛ እንደነበረ ብዙዋች ይስማማሉ፡፡
ዘመናዊ የሙዚቃ ትምህርቱን ከዕውቁ ሙዚቀኛ ነርሲስ ናልባንዲያን አና ከሌሎችም እንደቀሰመ የሚነገርለት ተፈራ አቡነወልድ የዛሬ ሃምሣ ዓመት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በተመሠረተበት ወቅትም “አፍሪካ ሃገራችን” የሚባለውን የናልባንዲያን ድርሰት ለድርጅቱ መሥራች አባቶችና ለሌሎችም ታዳሚዎች በቀረበበት ወቅትም ሙዚቀኞችን የመራው ተፈራ አቡነወልድ እንደነበረም ይታወሣል፡፡
ተፈራ አቡነወልድ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ባሕልና ቴአትር ክፍል እና በብሔራዊ ቴአትር ቤት በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግሏል፡፡
በ1928 ዓ.ም ኅዳር 3 በሰሜን ሸዋ ተጉለት ወግዳ መስቀለየሱስ በተባለ ሥፍራ የተወለደው ተፈራ አቡነወልድ ወደ ሙዚቃ ዓለም የተቀላቀለው ገና በ11 ዓመት ዕድሜው እንደነበር ተነግሯል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡