በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም ምረቃ የመሠረዝ ዜና ዙሪያ የተሰሙ ድምጾች


ቴዲ አፍሮ
ቴዲ አፍሮ
በቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም ምረቃ የመሠረዝ ዜና ዙሪያ ...
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:31 0:00

እንደተገኙ በተደወሉ የስልክ መሥመሮች አስተያየት የሰጡ ሰዎች ድምጽ ነው። ጉዳዩ የዕውቁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” የተሰኘው የሙዚቃ አልበም ምርቃት የመከልከል ዜና።

ድምጻዊው ይህንን አስመልክቶ በፌስቡክ ገጹ ይፋ ያደረገው መግለጫ እንዲህ ይላል።

“ነሐሴ 28 - 2009 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ልናካሂድ የነበረው የ“ኢትዮጵያ” አልበም ምርቃት አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ ተጠናቆ እና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች የመግቢያ ወረቀት ታድሎ ካበቃ በኋላ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ጉዳዩ ይመለከተኛል፤ የሚለው የመንግስት አካል መረሃ ግብሩን ማካሔድ እንደማንችልና ፍቃድ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ዝግጅቱ እንዳይካሄድ መከልከሉን ለክብሯን ወገኖቻችን ስናሳውቅ የተሰማንን ከፍተኛ ሀዘን በመግለጽ ነው።”

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ድምጽ ቀጥሎ ይሰማል። በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከተውን የመንግስት አካል ምላሽና የድምጻውን አስተያየት ለማካተት ያደረግንው ጥረት ግን ለጊዜው አልተሳካም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG