ማጉፉሊ እና ምክትል ፕሬዚደንታቸው ሳሚያ ሱሉሁ ሃሰን ዋና ከተማዋ ዳሬ ሰላም በሚገኘው ኡሁሩ ስቴዲየም ቃለ ማሃላቸውን ሲፈጽሙ በስፍራው የተሰበሰቡት ሰዎች በጭብጨባ ደስታቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚደንት ማጉፉሊ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት አጭር ንግግር በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት የገቡዋቸውን ቃሎች ተግባራዊ ለማድረግ በርትቼ እሰራለሁ ብለዋል
በዚህ ምርጫ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆየው ፓርቲ CCM ፕሬዚደንታዊና ምክር ቤታዊ ኣመራሩን ኣጽንቱዋል።
ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ፕሬዚደንታዊ ምርጫው ተጨበርብሩዋል በማለት ውጤቱን እንደማይቀበሉ ኣስተውቀዋል። የኣውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫው በሚገባ የተደራጀ ሆኖ ሳለ ግልጽነት ኣለመኖሩ ተቃዋሚዎች በሂደቱ ላይ ኣመኔታ እንዲያጡ ማድረጉን ገልጹዋል።
አዲሱ ፕሬዚደንት ማጉፉሊ ታንዜንያ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛትነት ነጸነቱዋን ካገኘት እ ኤ አ ከ1961 ወዲህ ኣምስተና ፕሬዚደንቱዋ ናቸው። ታንዜንያ በሌሎች ብዛት ያላቸው የኣፍሪካ ሃገሮች ከሚታየው በተለየ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማካሄድ ትታወቃለች። ፕሬዚደንት ጃካያ ኪክዌቴ ሁለቱን የስልጣን ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በሁዋላ በዚህ በዚህ ዓመት ወርደዋል። በይፋ በታወጀው የምርጫው ውጤት መሰረት ኣዲሱ ፕሬዚደንት ማጉፉሊ ለስልጣን የበቁት ዋናው ተፎካካሪያቸው ኤድዋርድ ላዋሳን ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ ሃምሳ ስምንት ለኣርባ ከመቶ በሆነ የድምጽ ብልጫ ኣሸንፈዋቸው ነው።