ማጥመጃ መርከብ የሚያፈላልገውን ቡድን እንዲቀላቀል ታይዋን፣ በቻይና ጥያቄ፣ የነፍስ አድን ተልዕኮ ቡድኗን ወደ ስፍራው አሰማርታለች፡፡
ታዋይን የባህር ዳርቻ ጠባቂ ጀልባዎቿን የቻይናን አፈላላጊ ቡድን እንዲቀላቀል ወደ ስፍራው የላከችው አሳሳቢ በሆነው የባህር ሰርጥ ውጥረት በነገሠበት ወቅት ነው፡፡
የሁለቱም ወገኖች ባለሥልጣናት የነፍስ አድን ጀልባዎችን የላኩት የቻይናውያን የዓሣ ማጥመጃ መርከብ ከተገለበጠች በኋላ መሆኑን የታይዋን ባህር ዳርቻ ጠባቂ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ሁለት አስክሬን ሲገኝ ሁለቱ የደረሰቡት አልታወቀም። ሁለት ሰዎች ግን በተገለበጠችው ጀልባ ውስጥ በህይወት ተገኝተዋል።
ታይዋን አራት የባህር ጠረፍ ጠባቂ መርከቦች ስትልክ ቻይናም ስድስት መርከቦችን በነፍስ አድን ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ልካለች።
ባለፈው ወር በኪንመን ደሴቶች አቅራቢያ ወደ ተከለከለው የታይዋን የባህር ወሰን ዘልቀው ለመግባት የሞከሩ ሁለት የቻይና ዜጎች፣ የታይዋንን የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ሲሸሹ ከባህር ሰጥመው ከሞቱ በኋላ፣ ቻይና አካባቢውን መቆጣጠር ጀምራለች፡፡
መድረክ / ፎረም