በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ የሶሪያን ህገ መንግሥት ለማርቀቅ ንግግር ይጀመራል አለ


የሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ምስል ሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ እአአ ግንቦት 10 ቀን 2021
የሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ምስል ሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ እአአ ግንቦት 10 ቀን 2021

የሶሪያ መንግሥት፣ ተቃዋሚዎችና የሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች በተባበሩት መንግሥታት አደራዳሪነት አዲስ ህገ መንግሥት ለማርቀቅ የሚያደርጉትን የሰባተኛው ዙር ንግግር በዚህ ሳምንት እንደሚጀምሩ ተገለጸ፡፡

ተባበሩት መንግሥታት አደራዳሪው ተወካይ ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን ጨምሮ የእስከዛሬዎች ንግግር ያለውጤት መበተናቸውን ገልጸዋል፡፡

የመንግሥትና የተቃዋሚ ድርጅቶች እርስ በርስ በመወቃቀስ ከሥምምነት አለመድረሳቸውንም አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግሥታት አደራዳሪ ልዩ ልዑክ ጌሪ ፐደርሰን በእርሳቸው ጉትጉታ በድርድሩ የመጨረሻ ቀናት መስተካከተል ያለባቸው ነገሮች ከተሟሉ ሦስቱም ወገኖች እንደገና ተገናኘተው ለመነጋገር መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም “ሦስቱ ልዑካን የተናገሩትን የሚያደርጉ ከሆነ ዘላቂ ለውጥ እንደምናይ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይሁን እንጂ በቀደሙት ስድስት ዙር ንግግሮች የተረዳሁት ነገር የንግግሩ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ አለመገመት ነው፡፡” ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት እኤአ በ2012 ለሶሪያ የሰላም ፍኖተ ካርታ ማውጣቱን ተነግሯል፡፡

ከዚህ ውስጥ አዲስ ህገ መንግሥት ማውጣትና በመንግሥታቱ ድርጅት ተቆጣጣሪነት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ባላፈው ግንቦት የራሳቸውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በማካሄድ መጠነ ሰፊ በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ጌሪ ፕርደስን በሁሉም ዘንደ ተቀባይነት ያለው ህገ መንግሥት ማጽደቅ ወይም አሁን ያለውን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ሲናገሩ

“ኮሚቴው እምነትና መተማመን ማምጣቱ ላይ እንዲሰራ በተደጋጋሚ ተናግሬያለሁ፡፡ የህገ መንግሥቱ ኮሚቴ የዚህን አሳሳቢነት በመረዳት ይህንን ማሳካት ግቡ ባደረግ ቁርጠኝነት ተነሳስቶ፣ በዚህኛው ዙር ሁኔታው ይህን የሚጠይቅ መሆኑን በመገንዘብ እንደሚሰራ ለማየት ተስፋ አደጋለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 11 ዓመት በዘለቀው የሶሪያ ውጊያ፣ ከ350 ሺ በላይ ሰዎች ሲሞቱ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉት ደግሞ በሃገር ውስጥና ወደ ውጭ አገር መፈናቀላቸው፣ 90 ከመቶ የሚሆነው የሃገሪቱም ህዝብ በድህነት ማጥ ውስጥ መግባታቸውን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG