በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብርቱ ፍልሚያ የሚደረግባቸው የ2024ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሚወስኑት ግዛቶች


ብርቱ ፍልሚያ የሚደረግባቸው የ2024ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሚወስኑት ግዛቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00

ብርቱ ፍልሚያ የሚደረግባቸው የ2024ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሚወስኑት ግዛቶች

በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ትኩረቱን አንድ ጊዜ የአንደኛው ፓርቲ በሌላ ጊዜ ደሞ የተፎካካሪው ፓርቲ እጩ በመፈራረቅ ወደሚያሸንፉባቸው ግዛቶች ይመልሳል።

እነዚህ ብርቱ ፍልሚያው የሚካሄድባቸው ግዛቶች፣ በተደጋጋሚ የአንዱ ፓርቲ ደጋፊ በቁጥር አይሎ ከሚታይባቸው የሚበዙት ግዛቶች በተለየ መልኩ የምርጫውን ውጤት ወደ አሸናፊው በማድረግ ወደ ዋይት ሀውስ ገብቶ አገሪቱን በፕሬዝዳንትነት የመምራት እጣ የሚገጥመው ሰው ማን እንደሚሆን ይወስናሉ።

ይህን መሰል ግዙፍ ተጽዕኖ የማሳደር ዕድል ያላቸው ጥቂት ግዛቶች እንደመሆናቸው የምርጫ ዘመቻዎች መጠኑ የበዛ ገንዘብ በእነኚህ ወሳኝ ግዛቶች ውስጥ ለሚያካሂዷቸው የምረጡኝ ዘመቻዎቻቸው ወጭ ያደርጋሉ። በተደጋጋሚ እንደታየውም ለእነኚህ ግዛቶች አሸናፊ የተመደቡት ድምጾች አጠቃላዩን የምርጫ ውጤት ስለሚወስኑ የምርጫ ዘመቻዎቹ ጠንካራ የምረጡኝ ቅስቀሳ ትኩረት ያደርጋቸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG