ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍጋኒስታን በሚካሄደው የምክር ቤት ምርጫ ሊወዳደሩ የነበሩ ሰው በምርጫ ዘመቻ ጽህፈት ቤታቸው ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት እንደተገደሉ የሄልማንድ ክፍለ ሀገር ባለሥልጣኖች ተናግረዋል።
ጃባር ኳህራማን ላሽካርጋህ ከተማ በሚገኘው የምርጫ ዘመቻ ጽህፈት ቤታቸው ላይ በደረሰ ፍንዳታ እንደተገደሉ የሄልማንድ አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ ኦማር ዝዋክ ገልፀዋል። በርካታ ሌሎችም በፍንዳታው እንደቆሰሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። የሄልማንድ የአስቸኳይ ጊዜ ሆስፒታል ሃኪም ሁለት ሰዎች እንደሞቱና ሥድስት እንደቆሰሉ ተናግረዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ