ዋሺንግተን ዲሲ —
ለሱዳን ስለሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ለመነጋገር በርሊን ላይ የተጠራው የዓለምቀፍ ለጋሾች ጉባዔ ዛሬ የርቀት ቪዲዮ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ዓለምቀፉን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጨምሮ በተለያዩ ችግሮች የተወጠረችው ሱዳን ከዚህ ጉባዔ ችግሯን ቀለል የሚያደርግ ውጤት አገኛለሁ ብላ ተስፋ አድርጋለች።
የአውሮፓ ህብረት ጀርመን ተመድ እና ሱዳን በጠሩት ውይይት ከአርባ የሚበልጡ ሃገሮች እንደሚሳተፉ ተጠብቋል።