በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍሬዲ በሞዛምቢክና ማላዊ ከ190 በላይ ሰዎችን ገደለ


ፍሬዲ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ከባድ አውሎንፋስና ዝናብ የፈጠረው ጉዳት ብላንታየር፤ ማላዊ
ፍሬዲ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ከባድ አውሎንፋስና ዝናብ የፈጠረው ጉዳት ብላንታየር፤ ማላዊ

ማላዊና ሞዛምቢክ ውስጥ "ፍሬዲ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ከባድ አውሎንፋስና ዝናብ ከ190 በላይ ሰዎችን መግደሉ ተነገረ፡፡

በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ አካባቢውን የደቆሰው ፍሬዲ ትናንት ሰኞ የማላዊ ከተማ በሆነችው ብላንታየር ውስጥ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡

ከባዱ ነፋስና ዝናብ ማላዊ ውስጥ በትንሹ 99 ሰዎች ሲገድል አጎራባቿ በሆነችው ሞዛምቢክ ውስጥ ያደረሰው የጉዳትና ሞት መጠን አለመታወቁ ተመልክቷል፡፡

“እስካሁን 30 አስክሬኖችን አግኝተናል” ያሉት አንድ የነፍስ አድን ሠራተኛ “ሌሎች ተጨማሪ ሰለባዎችን ለማግኘት እየፈለግን ነው’ ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

“በትንሹ 60 የሚሆኑ አስክሬኖች ብላንታየር ወደሚገኘው ማዕከላዊ ሆስፒታል መጥተዋል” ሲል ድንበር የለሹ የሀኪሞች ማህበር ማስታወቁም ተዘግቧል፡፡

የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሌሎች 200 ሰዎችም በሆስፒታሉ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ፍሬዲ በደቡባዊ አፍሪካ ንፍቀክበብ ከተመዘገቡ ከባድ አውሎ ነፋሶች አንዱ መሆኑም በዘገባው ተገልጿል፡፡

የዓለም ሚቲዮሮሎጂ ድርጅት ፍሬዲ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል አውሎ ነፋስ ሊሆን ይችላል ብሏል፡፡

ወደ ማላዊ ግዛት በመዝለቅ የመሬት መንሸራተትን ያስከተለ ከባድ ዝናብ ከማስከተሉ በፊት ፍሬዲ ባላፈው ቅዳሜ ማዕከላዊ ሞዛቢክን ማጥቃቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

ከባላፈው ወር አንስቶ በሞዛምቢክ፣ ማላዊና ማዳካስክርን የመታው ፍሬዲ በጠቅላላው ወደ 136 የሚደርሱ ሰዎችን መግደሉ ተዘግቧል፡፡

ባለሥልጣናት በሞዛቢክ የደረሰው የሰብሎች ውድመት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ ለውሃ ወለድ በሽታ መጋለጥን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

በማላዊ የሚገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማትም በታሪክ ገዳይ የሆነው የኮሌራ ወረርሽኝ አሁን የበለጠ ሊባባስ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG