በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

'የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች' ቆይታ ከአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር ዮናስ ላቀው ጋር


Dr Yonas Lakew
Dr Yonas Lakew

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የአእምሮ ሕክምና ማዕከል የሆነ አማኑኤል የአእምሮ ጤና ሆስፒታል ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በሃገሪቱ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይሁንና በሃገሪቱ ከአእምሮ ጤና ጋር ተያይዞ ያለው ዕውቀት ባለመዳበሩ ስለሕክምናውም ሆነ ስለሆስፒታሉ ሰፊ የሆነ አሉታዊ አመለካከት አለ፡፡ ይህንን የተገነዘቡት የሆስፒታሉ የአእምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ዮናስ ላቀው በቅርቡ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች የሚል መጽሃፍ ለገበያ አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ዮናስ ላቀው ታዲያ ብዙ ሰዎች በአማኑኤል የአእምሮ ሆስፒታል ታክመው ከዳኑ በኋላ እዛ መታከማቸውን መናገር ይፈራሉ ይላል ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድንገት እነዚህ ሰዎች ከሰው ለየት ያለ ነገር ሲናገሩም ሆነ ሲሰሩ ቢታዩ “እሱ/ እሷ ድሮስ ከአማኑኤል አይደል እንዴ የመጡት?” ይባላሉ ይላል ዶ/ር ዮናስ ላቀው፡፡ እንደውም ከነጭራሹም እዛ የምትሰሩት እራሳቹ ‘እብዶች አይደላቹ እንዴ?’ ተብዬም አውቃለሁ ይላል፡፡

ሙሉውን ቃለምልልስ ያድምጡት፡፡

'የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች' ቆይታ ከአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር ዮናስ ላቀው ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:06 0:00


XS
SM
MD
LG