የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ድኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ያቀረቡትን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ አደረገ። አቃቤ ሕግ ካቀረበባቸዉ ክሶች ሁለቱ ውድቅ የተደረገላቸው አቶ ታዬ፣ በዛሬው ዕለት ስድስት ኪሎ ከሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን አቤቱታ ቀደም ሲል የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን የፍርድ ውሳኔ በማፅናት ነው ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገው።
መድረክ / ፎረም