ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ክልሉን በፕሬዚዳትነት እየመሩ ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ባቀረቡጥ ጥያቄ መሰረት መሆኑ ታውቋል፡፡
የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ “የአመራር ለውጥ ያስፈለገው ወቅታዊውን ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለሽግግሩ እና ለሰላም ድርድር የሚስማማ ካቢኔ ማዋቀር አስፈላጊ በመሆኑ ነው” ብሏል።
በሌላ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እየወጡ እንደሚገኙ መረጃ እንዳላት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ተናገሩ፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ፣ ከሚታዩ ለውጦች ጋር ተያይዞ ሊነሳ አሊያም ሊጨምር እንደሚችልም ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።