በኬንያ፥ ሕገወጥ የጉልበት ሰጪ መድሃኒት መጠቀም ቅሌት መከሰት፥ ሀገሪቱ በአትሌቲክስ በአለም ገናና የሆነችበትን ታሪኳን እንዳያበላሽ ተሰግቷል። በተለይ አሁን በመጨረሻ በሁለት የቦስተን እና የቺካጎ ማራቶኖች ቀደም ሲል ደግሞ በስቶክሆልም፥ ፓሪስ፥ ሚላን እና ሊዝበን ያሸነፈችው Rita Jeptoo በተደረገላት ምርመራ ደሟ ውስጥ የተከለከለ ጉልበት ሰጪ መድሃኒት መኖሩ ከተረጋገጠ በሗላ ሁኔታው በእጅጉ አሳሳቢ ሆኗል።
በጠቅላላው 36 የኬንያ አትሌቶች ባለፉት ሁለት አመታት የተደረገላቸውን የደም ምርመራ ሳያልፉ ቀርተዋል።