በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳኑ አማፂ ‘የኢትዮጵያ አማፂ ወጋኝ’ ይላል


የኢትዮጵያው አማፂና ጁባ አስተባብለዋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:10:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሳልቫ ኪር መንግሥት የኡትዮጵያውን የሽምቅ ተዋጊ ነኝ የሚለውን አማፂ ቡድን የኢትዮጵያ የተባበሩት አርበኞች ግንባርን እየረዳ እየወጋኝ ነው ሲል ያወጣውን ስሞታ ሱዳን ትሪብዩን የሚባለው የሱዳን የኢንተርኔት ጋዜጣ ይዞ ወጥቷል፡፡

የተቃዋሚው የሱዳን ሕዝብ አርነት ንቅናቄ ኤስፒኤልኤም-አይኦ ቃልአቀባይ ኮሎኔል ጄምስ ሎኒ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የኢትዮጵያ የተባበሩት አርበኞች ግንባር ደቡብ ሱዳን ውስጥ ፊሻላ አካባቢ የጦር ሠፈር እንዳለው፤ በቅርቡም ማቲያንግ እና አጎክ አካባቢ ከመንግሥቱ ኃይሎች ጋር ሆኖ 2000 የሚሆኑ ተዋጊዎቹን አዝምቶበት እንደወጋቸው አመልክተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ኃይሎቻቸው የአፀፋ ጥቃት ከፍተው እንዳባረሯቸውና ከካከላቸውም የገደሏቸው እንዳሉ ኮሎኔል ሎኒ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ሳልቫ ኪር ለኢትዮጵያው አርበኞች ግንባር መሪ ለትዋት ፓል ቻይ ይህንን ዘመቻ እንዲያካሄዱበት አንድ ሚሊየን ዶላር እንደሰጧቸው የሚያረጋግጥ ሰነድ መያዛቸውንና ለኢትዮጵያ የስለላ አካላት መስጠታቸውን የኤስፒኤልኤም-አይኦ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሎኒ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ግን የሱዳን መንግሥት ጦር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ፊሊፕ አጉየርና የአርበኞች ግንባሩ መሪ አቶ ትዋት ፓል ቻይ ክሡ የሃሰት ውንጀላ ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG