ጁባ፤ አዲስ አበባ —
ያቋረጥነውን የሰላም ድርድር ለመቀጠል የፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርን መመሪያ እየጠበቁ መሆናቸውን የደቡብ ሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትርና የመንግሥት ተደራዳሪዎች ቃል አቀባይ አመልክተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ማኩየይ ሉዊዝ እንዳብራሩት ፕሬዝዳንቱ መመሪያውን የሚሰጡት የኢጋድ ዋና ፀሐፊ በሠነዘሩት አስተያየት ላይ ግልፅና የሚያረካ ምላሽ ካገኙ በኋላ ነው።
የደቡብ ሱዳን የሃይማኖት መሪዎች ግን ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ምክንያት ከመደርደር ተቆጥበው ወደ ሰላም ድርድሩ እንዲመለሱ ጥሪ አድርገዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ዛሬ ለፓርላማቸው ንግግር አድርገው እርሳቸው ፕሬዚዳንቱ እስከሆኑ ድረስ ማንኛውንም የሽግግር መንግሥት እንደሚቀበሉም አስታውቀዋል፡፡
እንዲሁም ጦርነቱን ሸሽተው ቀያቸውን ለመልቀቅ የተገደዱ ደቡብ ሱዳናውያን ውጊያው ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ታሕሳስ አንስቶ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው በብዛት መጉረፍ እንደቀጠሉ ነው።
የክረምት ወቅት እየገባ በመሆኑ ሁኔታው በስደተኞቹ ይዞታ ላይ የሚያሳድረው ጫና እንዳሳሰበው ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም አስታውቋል።
ለዝርዝሩ የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡