በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የደቡብ ሱዳን የአከባቢ ጥበቃ ሀይሎች ከተመድ የሠላም ጥበቃ ጋር ማቀናጀት ሉዓላዊነት አለማክበር አይደለም” የአሜሪካ ዲፕሎማት


ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ የአከባቢ ጥበቃ ሀይሎች ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠላም ጥበቃ ተልዕኮ ጋር ማቀናጀት የአገሪቱን ሉዓላዊነት ያለማክበር ተንኮል አይደለም ሲሉ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ተናገሩ።

በዩናይትድ ስቴትስ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት የቀረበ አንድ ረቂቅ በደቡብ ሱዳን የተመደቡ 4,000 የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ሀይሎች የመንግሥታቱ ድርጅት የሠላም ሀይሎች ጥበቃ ተልዕኮ እንዲሆኑ ሃሳብ ያቀርባል።

ረቂቁ የመንግሥታቱ ድርጅት የሠላም ጥበቃ ሀይሎች የጁባ አለምአቀፍ አይሮፕላን ጣብያና ቁልፍ የሆኑ የአገሪቱ አከባቢዎች እንዲጠብቁ ይላል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG