በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ፀበኞች አዲሳባ ገቡ


የደቡብ ሱዳን ፀበኞች - ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞ ምክትላቸው ሪያክ ማቻር የግጭት አካባቢዎች
የደቡብ ሱዳን ፀበኞች - ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞ ምክትላቸው ሪያክ ማቻር የግጭት አካባቢዎች



ደቡብ ሱዳን፣ ከተሞቿና ጎረቤቶቿ
ደቡብ ሱዳን፣ ከተሞቿና ጎረቤቶቿ

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የደቡብ ሱዳን ባላንጣ ወገኖች ማለትም የፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞ ምክትላቸው ሪያክ ማቻር ተወካዮች አዲስ አበባ ላይ ለመደራደር በወሰኑት መሠረት ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ገብተዋል፡፡

ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ወገኖቹ ለመደራደር መስማማታቸውን “የዲፕሎማሲ ጥረቱ ውጤት ነው” ብለውታል፡፡

በጥረቱ ውስጥ ኢትዮጵያ እንደ ጎረቤት ሃገርም እንደ አካባቢው ሃገሮች የጋራ ልማት ተቋሙ ኢጋድም ሰፊ ድርሻ መያዟን ቃል አቀባዩ አክለው ገልፀዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያ
ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያዊያኑን ወደ ሃገራቸው የመመለሱ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት አምባሣደር ዲና በጋምቤላ በኩል የገቡት፣ ትናንት፣ ሰኞና ዛሬም፣ ማክሰኞ ወደ ሃገር እንዲመለሱ የተደረገ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጠቅላላው 1229 መድረሱን አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ዜጎቹን ከጦርነት ቀጣና ለማስወጣት ሦስት አይሮፕላኖችን ማሠማራቱን አምባሣደር ግርማይ ገብረማርያም ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በቦር ከተማ የሚገኙት ዜጎችን ለማስወጣት ግን ከፀጥታ ሥጋት አንፃር በዚህ ሰዓት አይሮፕላን ማሣረፍ ስለማይቻል በተባበሩት መንግሥታት መጠለያ እንዲቆዩ መክረዋል።

አምባሣደር ግርማይ በተጨማሪ ወደ ኤርትራ ለመመለስ ለሚፈልጉ ዜጎች የተለየ የሊሴ ፓሴ ወረቀት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

ወደ ኤርትራ ሲመለሱ የደኅንነት ሥጋት ይደርስባቸው እንደሆን ተጠይቀው “ምንም የሚገጥማቸው ችግር የለም፤ እኛ ካሁን በፊት ያሉት ነገር አያገባንም። አሁን ህይወታቸውን የማዳን ጥያቄ ነው የሚሆነው። እንዴት መጡ? ምንስ ነበሩ? የደኅንነት ችግር አለባቸው ወይ? ቀለማቸውን አንጠይቅም፡፡ መዝግበን እንቀበላቸዋለን፤ አለቀ፡፡ አሁን ያለው የመጀመርያ ዓላማችን ህይወታቸው እንዲድን መርዳት ነው፡፡ ፖለቲካዊ አስተሳሰባቸውም ይሁን ሌላ አሁን አያስፈልገንም።” ብለዋል በደቡብ ሱዳን የኤርትራ አምባሣደር ግርማይ ገብረማርያም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG