በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን ውስጥ ጎሣ የለየ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ


ጆንግሌይ ክፍለሃገር - የሰላማዊው ሰው መፈናቀል
ጆንግሌይ ክፍለሃገር - የሰላማዊው ሰው መፈናቀል

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ከዋና ከተማይቱ ጁባ በስተሰሜን ያለው የሃገሪቱ ግዛት ከቁጥጥሩ መውጣቱ ተገለፀ፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዋች
ሂዩማን ራይትስ ዋች

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ከዋና ከተማይቱ ጁባ በስተሰሜን ያለው የሃገሪቱ ግዛት ከቁጥጥሩ መውጣቱ ተገለፀ፡፡

ሳልቫ ኪር /ፎቶ ፋይል/
ሳልቫ ኪር /ፎቶ ፋይል/
በሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ውስጥ የተባባሰው ውጊያ ሃገሪቱን ወደ በለጠ መከፋፈል ሊወስዳት እንደሚችል እየተሰጋ ነው ሲሆን አሁን ያለውን የሁከት ሁኔታ የሚሸሹ ሲቪሎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ይሰማል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ጎሣ የለየ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑንና በተለይ የሪያክ ማቻር የሆነው የኙዌር ጎሣ አባላት ዒላማ መደረጋቸውን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አስታውቋል፡፡

ሪያክ ማቻር /ፎቶ ፋይል/
ሪያክ ማቻር /ፎቶ ፋይል/
ይህ በእንዲህ እንዳለ “ጁባ ላይ የቤተመንግሥት አብዮት” መካሄድ አለበት ሲሉ ተቃዋሚው የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪያክ ማቻር የሳልቫ ኪር አስተዳደር እንዲወገድ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ከማቻር ጋር ቃለምልልስ ያካሄደው ራዲዮ ፍራንስ አንተርናስዮናል አመልክቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ልዑክ - ኡንሚስ
የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ልዑክ - ኡንሚስ
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋና ከተማይቱ ጁባ ውስጥ ያለው ሁኔታ በተወሰነ ደረጃ መረጋጋቱንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች በመጠኑ መንቀሳቀስ የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩን የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ፋራህ ሃቅ ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG