በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን - ተፈራረሙ

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሠላም ስምምነቱን ሠነድ ሲፈርሙ፤ ከጀርባ - የኬንያ ፕሬዚዳንት ኢሁሩ ኬንያታና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ - ጁባ፤ ደቡብ ሱዳን - ነኀሴ 20/2007 ዓ.ም
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሠላም ስምምነቱን ሠነድ ሲፈርሙ፤ ከጀርባ - የኬንያ ፕሬዚዳንት ኢሁሩ ኬንያታና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ - ጁባ፤ ደቡብ ሱዳን - ነኀሴ 20/2007 ዓ.ም

የደቡብ ሱዳን ፕሬዘዳንት ሣልቫ ኪር ብዙ ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውን የሰላም ስምምነት ዛሬ ጁባ ከተማ ውስጥ ፈርመዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢጋድ ፕለስ ተብሎ የተሰየመው ቡድን ስለ ደቡብ ሱዳን የፀጥታ ሁኔታ ውይይት ሲያካሂድ /ፎቶ ፋይል - አዲስ አበባ/
ኢጋድ ፕለስ ተብሎ የተሰየመው ቡድን ስለ ደቡብ ሱዳን የፀጥታ ሁኔታ ውይይት ሲያካሂድ /ፎቶ ፋይል - አዲስ አበባ/

የደቡብ ሱዳን ፕሬዘዳንት ሣልቫ ኪር ብዙ ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውን የሰላም ስምምነት ዛሬ ጁባ ከተማ ውስጥ ፈርመዋል።

ይህም ለበርካታ ወራት የዘለቀውን አስከፊ የርስ በርስ ውጊያ ያበቃል ተብሎ ይታመናል።

ስምምነቱ የተፈረመው አንድ ዓመት ከስምንት ወር ውጊያ በኋላ ነው፡፡

የሽምቅ ተዋጊዎቹ መሪ ሪያክ ማቻር እና የቀድሞው የፖለቲካ እሥረኛ ፓጋን አሙም ስምምነቱን ከአሥር ቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ ፊርማቸውን አኑረውበት ነበር፡፡

ሚስተር ኪር በፊርማው ሥነ-ሥርዓት ላይ ለተሰበሰቡ የአካባቢው ሃገሮች መሪዎች ሲናገሩ አሁንም በአንዳንድ የስምምነቱ አንቀፆች ላይ “ጠንካራ ተቃውሞ አለኝ” ብለዋል፡፡

እንዲሁም አንድ ነጥብ ላይ ስምምነቱን ዛሬ ሊፈርሙ እንደማይችሉ ጠቁመው ነበር፡፡

በፊርማው ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ፣ የኬንያና የዩጋንዳ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG