በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ድርድር በ “ስቱፒድ” ምክንያት ተቋረጠ


ማሕቡብ ማአሊም - የኢጋድ ዋና ፀሐፊ
ማሕቡብ ማአሊም - የኢጋድ ዋና ፀሐፊ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ትብብር ተቋሙ ኢጋድ አንድ ባለሥልጣን በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በተቃዋሚው መሪ ሪያክ ማሻር ላይ የዘለፋ ቃል ሠንዝረዋል በሚል በሁለቱ ወገኖች መካከል ይካሄድ የነበረው ውይይት ተቋርጧል፡፡

ውይይቱ የተስተጓጎለው ተቃዋሚዎቹ በሰዓቱ ባለመገኘታቸው ጭምር ነው ሲሉ አንድ የመንግሥቱ ቃል አቀባይ የተናገሩ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ደግሞ የተሟላ ውክልና ስለመኖሩ ሥጋት አለን ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎቹ ባለፈው ዕሁድና በማግስቱም ሰኞ በናስር ከተማ ላይ ጥቃት አድርሰዋል ሲሉ የአፐር ናይል ግዛት ባለሥልጣናት ክስ አሰምተዋል፡፡

ጥቃቱ በደረሰ ወቅት በመረጋጋቱ የተበረታቱ ሰላማዊ ነዋሪዎች ወደ ከተማይቱ እየተመለሱ እንደነበረ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል፡፡

የተቃዋሚዎቹ ቃል አቀባይ ግን የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ክሥ “ሃሰት ነው” ብለው እነርሱ ያደረጉት የተፈፀመባቸውን የከባድ መሣሪያ ድብደባ መመከትና ይዞታቸውን መከላከል ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሌተና ጀነራል ዮሃንስ ገብረሚካኤልና ባን ኪ-ሙን
ሌተና ጀነራል ዮሃንስ ገብረሚካኤልና ባን ኪ-ሙን
በሌላ በኩል ደግሞ ደቡብ ሱዳን ለሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን የሰላም ጥበቃ ልዑኩ - ኡንሚስ አዛዥ እንዲሆኑ ኢትዮጵያዊው ሌተና ጀነራል ዮሃንስ ገብረሚካኤል ተሹመዋል፡፡

ፊሊፕ አሊዩ ከጁባ የላከውንና ከሌሎች ምንጮች የደረሱንን ዘገባዎች ሰሎሞን አባተ አቀናጅቶ ያቀርባቸዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG