በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የደህንነት ስምምነታቸውን አደሱ


የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን፣ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስትር ሺን ዋን ሲክን
የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን፣ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስትር ሺን ዋን ሲክን

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ እየጨመረ የመጣውን የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር እና የሚሳኤል ስጋት በጋራ ለመቀልበስ የደህንነት ስምምነታቸውን እንደገና አድሰዋል።

ሁለቱ ወገኖች በተጨማሪም ጃፓንን ጨምሮ የሶስትዮሽ የመከላከያ ልምምድ የሚያደርጉበትን መንገድ ተወያይተዋል።

የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን ለዓመታዊ ውይይት ሶል የተገኙ ሲሆን፣ የአገሪቱን የመከላከያ ሚኒስትር ሺን ዋን ሲክን ጨምሮ ከሌሎች ባለሥልጣናትም ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በተለይም ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ጥቃት እንዳትፈጽም የሚከላከሉበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል። ይህም እየጨመረ በመጣው የሰሜን ኮሪያ የጦር መሣሪያዎች ሙከራ እና ደቡብ ኮሪያ ከአጋሯ አሜሪካ ጋር የምታደርገው ወታደራዊ ልምምድ እየተጠናከረ በመምጣቱ ነው ተብሏል።

ሁለቱ ወገኖች ከአሥር ዓመት በኋላ የታደሰ ነው የተባለውን የደህንነት ስምምነት መፈራረማቸው ታውቋል።

ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ ላይ የኑክሌር ጥቃት ብትሰነዝር፣ አሜሪካ የኑክሌር ኃይሏን ጨምሮ ሙሉ ወታደራዊ አቅሟን በማሰማራት ደቡብ ኮሪያን እንደምትከላከል ስምምነቱ አስቀምጧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG