በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ኮሪያ  ፕሬዝዳንት ዩን ከእስር ተለቀቁ 


የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል
የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል

የደቡብ ኮሪያ ፍርድቤት በክስ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የእስር ማዘዣ እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ አቃቢ ህግ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ላለመጠየቅ በመወሰኑ ዛሬ በሴኡል ከሚገኘው እስርቤት ተለቀዋል፡፡

ዮን በእአአ ታህሳስ 3 ቀን ባሳለፉትና ለአጭር ጊዜ በቆየው የማርሻል ህግ ምክንያት ከስራቸው እንደታገዱ የሚቆዩ ሲሆን በአመፅ የቀረበባቸው ክስም እንዳለ ይቆያል ተብሏል፡፡

የወንጀል ጉዳዩ በስልጣን ላይ በሚኖራቸው ቆይታ ዙርያ ክሚታየው የፍርድ ሂደት የተለየ ሲሆን በህገ-መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ወደ ሥራ ይመለሱ ወይም ከሥልጣናቸው ይነሱ በሚለው ጉዳይ ላይ በሚቀጥሉት ቀናት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG