በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሰሜን ኮሪያ የከዱ ዜጎች ወደ ሀገራቸው የፊኛ መልዕክትና ሙዚቃ ላኩ


ፎቶ ፋይል፦ የፊኛ ዘመቻዋን ያስጀመረው ከሰሜን ኮሪያው የከዱት ሰዎች ቡድን መሪ ፓርክ ሳንግ-ሃክ
ፎቶ ፋይል፦ የፊኛ ዘመቻዋን ያስጀመረው ከሰሜን ኮሪያው የከዱት ሰዎች ቡድን መሪ ፓርክ ሳንግ-ሃክ

ከሰሜን ኮሪያ የከዱ ዜጎች ቡድን፣ ጸረ-ሰሜን ኮሪያ በራሪ ወረቀቶችን የያዙ ፊኛዎችን ዛሬ ሐሙስ ማለዳው ላይ ወደ ሰሜን ኮሪያ መልቀቅ ጀመሩ፡፡

ከሰሜን ኮሪያው የከዱት ሰዎች ቡድን መሪ ፓርክ ሳንግ-ሃክ ከድንበሩ በስተደቡብ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ከፖቼዮን ከተማ በኮምፒውተሮች ላይ የሚሰኩ መረጃ አቃፊ ወይም የዩኤስቢ ስቲኮች እና የደቡብ ኮሪያ ሙዚቃዎችን የጫኑ ፊኛዎችን መልቀቃቸውን ተናግረዋል።

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ወር ቆሻሽ የተጫነባቸውን ወደ 1,000 የሚጠጉ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ ሰማዮች መልቀቋ ይታወቃል።

ከግንቦት 25 በኋላ ሰሜን ኮሪያ የፊኛ ዘመቻዋን ለጊዜው እንደምታቆም ገልጻለች፡፡ ይሁን እንጂ ግን በደቡብ ኮሪያ የተላኩ ተጨማሪ ፀረ የሰሜን ኮሪያ በራሪ ወረቀቶችን ካገኘች አጸፋውን በመመለስ እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

ለቆሻሻ ፊኛዎቹ ትንኮሳ ምላሽ፣ ደቡብ ኮሪያ እኤአ በ2018 በኮሪያዎች መካከል የተደረሰበትን ወታደራዊ ስምምነት በማቋረጥ፣ የደቡብ ኮሪያ ጦር በድንበር አካባቢ የሚያደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እንደገና እንዲቀጥል ፈቅዳለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG