ስማቸው እንዳይጠቀስ በመጠየቅ ያነጋገሩን የከተማዋ ነዋሪዎች በአምስቱ ዓመት መርሃ ግብር መሰረት ህዳር አንድ መጀመር የነበረበት የሞጣ-እስቴ መንገድ ግንባታ ተቀይሮ ከማህደረ ማሪያም እስከ ደብረ ታቦር እንዲሆን በመደረጉ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንደወጣ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገልጸዋል።
ሆኖም የዞኑ ሃላፊ አቶ እዘዝ ዋሴ ጋዜጠኛ እናመጣለን በማለት ሲያታልሉን ቆይተው፣ ልዩ ሃይልና ፌደራል ፖሊስ በከተማዋ አሰማሩ ብለዋል። የህዝቡ ተቃዉሞ ሰላማዊና የልማት ጥያቄ ላይ ያተኮረ መሆኑን በተለይ የመጡት የልዩ ሃይል ተወካዮች የተገነዘቡ ቢሆንም ከወረዳው ባለስልጣናት የተነገራቸው ግን ሕዝቡ የመንግስት ተቋማትን እየደበደበ ነው የሚል ነው ብለዋል።
ከአንድ ቀን ዉሎ በሁዋላ ግን ወጣት ልጆች ሳይቀሩ ወንድ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ እየታፈሰ ወደ እስር ቤት መወሰዱን፣ ቃል የሰጡን ግለሰብም በሽሽት ጫካ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ዜናውን ያጠናቀረው አዲሱ አበበ ከመንግስት ባለስልጣናት ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ተለያዩ ቢሮዎች ስልክ ደውሎ ነበር። ስብሰባ ላይ እንዳሉ በመግለጽ እስካሁን መልስ አልሰጡም፣ እንደደረሰን እንዘግባለን።
ዘገባውን ያዳምጡ።