በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ክልል ግጭት ባሉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች እንደገና እንዲፈተኑ ተወሰነላቸው


በደቡብ ክልል ግጭት ባሉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች እንደገና እንዲፈተኑ ተወሰነላቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:50 0:00

በደቡብ ክልል ጦርነትና ግጭት ባሉባቸው እና በነበሩባቸው አከባቢዎች ኾነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤታ ያላመጡ ተማሪዎች እንደ አዲስ እንዲፈተኑ ተወሰነላቸው። ውሳኔውን የሰጠው ትምሕርት ሚኒስቴር መሆኑን የክልሉ ትምሕርት ቢሮ ገልጿል።

የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ከተባሉ ከ2ሺሕ በላይ ተማሪዎች ውስጥ አስተያየታቸውን ለቪኣኤ የሰጡ ተማሪዎች በውሳኔው መደሰታቸውን ገልፀው፤ ካለፈው ውጤት የተሻለ ለማስመዝገብ ከወዲሁ እየተሰናዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ችግር ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የሌሎች ክልል ተማሪዎች እንዲፈተኑ ተወስኖላቸው በደቡብ ክልል በተለይም የኮንሶ ዞን፣ የአማሮ እና የአሌ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች አለመካተታቸውን በመግለፅ ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን አቤቱታ መዘገባችን አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG