በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ክልል ተከታታይ ድርቅ ያስከተለው ረኀብ ሰዎችንና እንስሳትን እየገደለ መኾኑ ተገለጸ


በደቡብ ክልል ተከታታይ ድርቅ ያስከተለው ረኀብ ሰዎችንና እንስሳትን እየገደለ መኾኑ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00

• ከ337 ሺሕ በላይ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ ይሻሉ
በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል፣ ለድርቅ የተጋለጡ አርብቶ አደሮች፣ በቂ ሰብአዊ ርዳታ እንዳልቀረበላቸውና ከብቶቻቸውም እየሞቱባቸው እንደኾነ አስታወቁ። በምግብ እጥረት የተዳከሙት አርሶ አደሮቹ፣ ለበሽታ መጋለጣቸውንና አንዳንዶቹም በተያያዥ ጉዳቶች እየሞቱ መኾኑን ተናግረዋል።
የክልሉ አርብቶ አደሮች ጉዳይ ቢሮ እንደገለጸው፣ ከ400ሺሕ በላይ አርብቶ አደሮች፣ በክልሉ ለተከታታይ ዓመታት ለዘለቀው ድርቅ ተጋላጭ መኾናቸውን ገልጿል። “በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው የለም፤” ያሉት የቢሮው ሓላፊ አቶ ሎሬ ካኩታ፣ ከ70ሺሕ በላይ ከብቶች መሞታቸውን አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG