ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በከባድ ዝናብ የተነሳ የተፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ ሦስት መቶ አርባ አንድ ሰዎች ሲሞቱ በብዙ ሺህ የተቆጠሩ ነዋሪዎች የመጠለያ ኤሌክትሪክ እና ውሃ ችግር ውስጥ ወድቀዋል።
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በጎርፉ ለተጎዱት የሀገሪቱ ምስራቃዊ የጠረፍ አካባቢው ነዋሪዎች አስቸኳይ እርዳታ የሚውል ገንዘብ እንደሚለቅቅ አስታውቋል።
ፕሬዚዳንቱ ሲሪል ራማፎሳ የአጣዳፊ አደጋ ቀጣና ብለው ላወጁት አካባቢ ስድሳ ስምንት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዶላር ለአስቸኳይ እርዳታ መመደቡን የገንዘብ ሚኒስቴሩ አስታውቆ፣ ተጨማሪ ብዙ ሚሊዮን ዶላር ይመደባል ብሏል።
የክዋዙሉ ናታል ክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ እንዳስታወቁት በጎርፍ አደጋው አርባ ሺህ ሰባት መቶ ሰው ጉዳት ላይ ወድቋል።