በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤኤንሲ በራማፎሳ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ


ኤኤንሲ በራማፎሳ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:24 0:00

በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ የተሰየመ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሰሪል ራማፎሳ ‘ሕግ ሳይጥሱ አይቀረም እናም ቀርበው መልስ መስጠት አለባቸው’ የሚል ሪፖርት ካወጣ በኋላ ፓርቲያቸው ኤኤንሲ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።

ራማፎሳ በገጠር ቤታቸው በሚገኝ ሶፋ ውስጥ ተደብቆ የነበረን ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ጉዳይ በተመለከተ ቀርበው መልስ መስጠት አለባቸው ብሏል አጣሪ ቡድኑ።

“ፋርም ጌት” እይተባለ የሚጠራው ቅሌት ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ ጥሪ በአገሪቱ እንዲሰማ አድርጓል።

የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከማድረጉ በፊት የተናገሩት የኤኤንሲ ሊቀመንበር ግዌድ ማንታሼ እንዳሉት የአጣሪ ቡድኑ ግኝቶች በሚገባ መታየት አለባቸው።

አጣሪ ቡድኑ ተሰረቀ የተባለው ገንዘብ ከየት እንደመጣ፣ መጠኑንን በተመለከተ እንዲሁም ለታክስ ሪፖርት ተደርጎ እንደሁ ጥያቄዎች አሉ ብሏል።

ራማፎሳ እንደሚሉት ግን ገንዘቡ የመጣው ከሶስት ዓመት በፊት በገና ዕለት ለአንድ ሱዳናዊ ነጋዴ 20 ጎሾችን ሸጠው ነው። ሽያጩ በተከናወነበት ወቅት ግን በቦታው አልነበርኩም ብለዋል። ግለሰቡ ለ20 ጎሾች 580 ሺህ ዶላር መክፈሉንም አስታውቀዋል።

የቀድሞ የሥለላ ኃላፊ የነበሩት አርተር ፍሬዘር ነበሩ ከ4 እስከ 8 ሚሊዮን ዶላር ከራማፎሳ ቤት ከሚገኝ ሶፋ ውስጥ ከተደበቀበት መሰረቁን ይፋ ያደረጉት። ፍሬዘር እንደሚሉት ገንዘቡ የተሰበሰበው በራማፎሳና በአማካሪያቸው ቤጃኒ ቹኬ ወደ መካከለኛው ምሥራቅና አፍሪካ አግርሮች ባደረጓቸው ጉዞዎች ወቅት ነበር።

በኬፕታውን የአግሊካን ቤተ ክርስቲያ ሊቀ-ጳጳስ የሆኑት ታቦ ማክጎባ ሰዎች ለፍርድ ከምቸኮላቸው በፊት የምርመራው ውጤት እስከሚጠናቀቀ እንዲታገሱ ጥሪ አድርገዋል።

የአንድ የጸረ ሙስና ተቋም ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዌይን ዱቨኔጅ በበኩላቸው፣ “ከፕሬዚዳንቶች ብዙ እንጠብቃለን፣ ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን መልቀቅ አለባቸው፣ ኤኤንሲም ብዙ ችግሮች አሉበት” ሲሉ ተደምጠዋል።

የፓርላማ አባላት ሪፖርቱን ለማጽደቅና ፕሬዚዳንቱን ለጥያቄ ማቅረብን በተመልከተ ማክሰኞ ድምጽ እንድሚሰጡ ይጠበቃል።

ለአንድ የአገር ውስጥ ቴሌቭዥን ቃለ መጠይቅ የሰጡት የኤኤንሲው ማንታሼ ራማፎሳ ሥልጣን ለመልቀቅ አስበዋል መባሉን ሃስት ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አሁንም ከደሙ ንጹህ ነኝ ማለታችውንና ቃል አቀባያቸውም ራማፎሳ ለአገራቸው የሚበጀውን እያደርጉ ነው ሲሉ መናገራቸውን ቪኪ ስታርክ ከኬፕታውን የላከችው ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG