በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሮናቫይረስ በደቡብ አፍሪካ


ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው በሀገር ውስጥ ከአንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው የተላለፈ የኮሮናቫይረስ በሽታ መኖሩን ገልፃለች። አንድ በሽተኛ መኖሩን ከአንድ ሳምንት በፊት ካስታወቀች በኋላ ነው በሀገር ውስጥ የተላለፈ የኮሮናቫይረስ በሽታ መኖሩን የገለፀችው።

እስካሁን ባለው ጊዜ ከሀገሪቱ 9 ክፍለ-ግዛቶች፣ ቢያንስ በአምስቱ 17 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ስዎች መኖራቸው ታውቋል።

በሌላ ዜና ደግሞ የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ውሀን ያሉትን ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ 122 ደቡብ አፍሪካውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል። ውሀን ኮሮናቫይረስ የፈለቀባት የቻይና ከተማ መሆኗ ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG