በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 አዳዲስ ገደቦች በደቡብ አፍሪካ


የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፖሳ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፖሳ

ከባድ የኮቪድ-19 ሦስተኛ ዙር ስርጭት ማዕበል እየታገለች ባለችው በደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፖሳ በከፍተኛ ፍጥነት ተላላፊ የሆነውን ዴልታ ኮሮናቫይረስ ለመግታት በርከት ያሉ አዳዲስ ገደቦችን አውጀዋል።

"ይሄ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እጅግ በጣም አደገኛ በሆነ ፍጥነት እየተዛመተ ነው፥ ባንድ ጊዜ ብዙ ሰው ሊታመም እና ህክምና ሊያስፈልገው ይችላል፤ ስለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማደረግ እንደሚያስፈልግ አሳስባለሁ " ብለዋል።

ህዝባዊ ስብሰባ መከልከሉን፣ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን፣ አልኮል መጠጥ ንግድ እና ምግብ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦ መመገብ እንደሚከለከል እና ይህን ደንብ የሚጥሱ ከባድ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጆሃንስበርግ እና ፕሪቶሪያ ከተሞች ወደሚገኙባት ጉዋቴንግ ክፍለ ሃገር ለመዝናናት መጓዝ ለአስራ አራት ቀናት ተከልክሏል።

ከአፍሪካ ሃገሮች መካከል ከሁሉም በከበደ ደረጃ በኮቪድ-19 በተጠቃችው በደቡብ አፍሪካ በአሁኑ ወቅት ከአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ያሉ ሲሆን ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ብቻ ከ18,000 በላይ ትናንት 150,00 አዲስ ተያዦች መገኘታቸውን የሀገሪቱ የተላላፊ በሸታዎች ተቋም አስታውቋል። እስካሁን በኮቪድ ምክንያት 59,900 ሰዎች መሞታቸውንም የተቋሙ መረጃ ያመለክታል።

እጅግ ከባድ የኮቪድ ስርጭት ማዕበል ውስጥ ነን፥ አሁን እንደምናየው ከሆነ ያሁኑ ካለፉት ከሁለቱ የየሚብስ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ ትናንት በብሄራዊ ቴሌቭዢኑ ባደረጉት ንግግር ዴልታ የተባለው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ባሁኑ ወቅት ከዘጠኙ ክፍላተ ሃገር አምስቱ ውስጥ መታየቱን አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ለኮሮናቫይረስ ከተጋለጡት የብሪታንያ ጄንኔራል ኒክ ካርተር ጋር ባለፈው ሳምንት በአንድ ስብሰባ የተገናኙ በርካታ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመከላከያ ባለሥልጣናት ራሳቸውን ለይተው እየቆዩ መሆናቸው ተዘገበ።

XS
SM
MD
LG